Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

መዝናኛ

ነጻ አስተያየት

ሙዚቃዎች

ስፖርት

ጥበብ

ዜና

ቪዲዮዎች

» » » አይዟችሁ፤ ዘንዶው አይድንም! መስቀሉ አየለ

አይዟችሁ፤ ዘንዶው አይድንም! መስቀሉ አየለ

ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው እንዲሉ የወሬ ውዥንብር ነዝተው የሰውን ሰላም በመንሳት ደመወዝ የሚበሉ የቀን ጅቡ ተቀጣሪዎች ሰሞኑን በከፈቱት በአስር ሽዎች የሚቆጠር ተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት በሚረጩት ወሬ የተነሳ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በጥፍራቸው ቆመው የሚጠብቁ አንዳንድ ወገኖቻችን ጥርጣሬና ስጋት ገብቷቸዋል።  


ሆኖም ግን አሁንም በድጋሜ እንላለን፤የቀን ጅቡ ከዚህ በኋላ ነፍስ ዘሮ ጉልበት ገዝቶ ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ይደርስ ዘንድ መለስ ዜናዊ ዳግም ተሰቅሎ "ሊያድነው" ይገባል።

በርግጥ ለብዙዎቹ ወገኖቻችን ስጋቱን እንዲጋሩ ምክኛት የሆናቸው ጠ/ሚሩ ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ በተደጋጋሚ ወደ ሚዲያ በመረብ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጥ የነበረ በመሆኑና ነገር ግን ከአሜሪካን ጉብኝት መልስ ከሚዲያ የመራቁ ነገር ነው።  

ሆኖም ግን በተጨባጭ መታወቅ ያለበት አንድ ነገር አገሪቱ ውስጥ በየቦታው እየተፈጠረ ያለው አናርኪዝምና የቀን ጅቡ ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብና መሳሪያ ጭምር ውስጥ ውስጡን በመርጨት ቀውሱን በማባባስ እረገድ አሉታዊ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ፤ ይህንን ነገር አፈጣኝ ምላሽ በመስጠት ከስር ከስር እየተከታተሉ የመፍታቱ ሃላፊነት በራሱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ስለወደቀ ከዚህ ቡኋላ ቶሎ ቶሎ ወደ ህዝብ በመቅረቡ እረገድ የትወሰነ መለሳለስ እንደሚኖር ማወቅ ያለብን ሲሆን ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ነቅቶ በመጠበቁ ግን የሁላችንም የትግል ድርሻ ይሆን ዘንድ የግድ ነው።

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply