Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

መዝናኛ

ነጻ አስተያየት

ሙዚቃዎች

ስፖርት

ጥበብ

ዜና

ቪዲዮዎች

"በዘር እንዳትለያዩ ፤ በሀይማኖት እንዳትለያዩ ኢትዮጵያዊነታችሁን ጠብቁ" ቴዲ አፍሮ

ቴዲ አፍሮ
"በዘር እንዳትለያዩ ፤ በሀይማኖት እንዳትለያዩ ኢትዮጵያዊነታችሁን ጠብቁ" ቴዲ አፍሮ (Teddy Afro)
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም 
ፍቅር ያሸንፋል!!


ኢህአዴግ እስካሁን የርዕዮተ ዓለም ለውጥ አለማድረጉን ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ተናገሩ ኢህአዴግ የርዕዮተ ዓለም ለውጥ አላደረገም

 ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ

(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እስካሁን የርዕዮተ ዓለም ለውጥ አለማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚህ ወቅት ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ኢህአዴግ እስካሁን የርዕዮተ ዓለም ለውጥ አለማድረጉን ጠቅሰው፥ ድርጅቱ በጥልቅ ተሃድሶ መስመር ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢህአዴግ በሂደት ራሱን እያሻሻለና ተሃድሶ እያደረገ እዚህ መድረሱን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በአዳዲስ ሃሳቦች የሚስተዋለውን ፍላጎት ለመመለስ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ድርጅቱ በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤ በተወያየባቸው አጀንዳዎች በመግባባት መለያየቱን ጠቅሰው፥ በኢህአዴግ ልዩነት አለ በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረት የለውም ብለዋል።

በሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አሁን የመጣውን ለውጥ ሙሉ በሙሉ የተቀበሉና ያልተቀበሉ ግለሰቦች እንጅ እንደ ድርጅት ልዩነት እንደሌለም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለውጡን አልተቀበለም በሚል የሚቀርበው ወቀሳ አግባብ አለመሆኑንም አንስተዋል።

በህወሓት ውስጥ ለውጡን ደግፈው ለህዝቡ ሰላምና ብልጽግና የሚሰሩ አመራሮች የመኖራቸውን ያክል ለውጡን ያልደገፉ እንዳሉም አስረድተዋል።

ይህ ለውጥን ያለመቀበል ጉዳይ ግን በአራቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ የሚታይ መሆኑንም ነው የገለጹት፤ በጉዳዩ ላይ ህወሓት ብቻውን ሊወቀስ እንደማይገባ በመጥቀስ።

ቀጣዩ ምርጫና የኢኮኖሚ አሻጥር፥ በኢህአዴግ ምክር ቤት ባለው መቀመጫ በህዝብ ብዛት ቁጥር እየተሰራ አይደለም በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፥ ኢህአዴግ ግንባር ከመሆኑ አንጻር አራቱ ድርጅቶች በእኩል ድምጽና በመግባባት ተስማምተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም አንዱ የበላይ አንደኛው የበታች በመሆን አይሰሩምም ነው ያሉት በምላሻቸው።

በቀጣይ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያም ኢህአዴግ የምርጫ ጊዜውን የማራዘም ሀሳብ የለውም ብለዋል።

መንግስት ምርጫው ያለ ምርጫ ኮረጆ በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በታገዘ መንገድ በታቀደለት ጊዜ እንዲካሄድ ፍላጎቱ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ አንጻርም ሁሉም የሚያምንበትና ተዓማኒነት ያለው የምርጫ ተቋም እንዲፈጠር እንሰራለንም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በሃገሪቱ የኢኮኖሚ አሻጥር መስተዋሉን ጠቅሰው፥ ለዚህ አሻጥር መፍትሄ የሚያፈላልግ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱንም አውስተዋል።

ይህ የኢኮኖሚ አሻጥር ህዝቡን የታየው ለውጥ በታሰበው መልኩ እየሄደ አይደለም የሚል አንድምታ እንዲይዝ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

በዚህ የኢኮኖሚ አሻጥር ሳቢያ ወደ ኢኮኖሚው መፍሰስ የነበረበት በርካታ ገንዘብ በግለሰቦች እጅ ስር እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሃገራት ገንዘብ መውጣቱን በተመለከተም፥ መንግስት የተባለውን ገንዘብ የማስመለስ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው ለሂደቱ ሁሉም ተባባሪ እንዲሆኑም ጠይቀዋል።

ፕራይቬታይዜሽን እና የትምህርት ፍኖተ ካርታ፥ አንዳንድ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በፕራይቬታይዜሽን ለማዘዋወር በሚደረገው ሂደት በተቋቋመው ከሚቴ ውስጥ ከሙያቸው ውጭ የተመደቡ ሰዎች ጉዳይ እንዴት ይታያል የሚል ጥያቄም ተነስቶላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በአካሄዱ ግልጽነትን ለማስፈንና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተሳተፈበት እንዲሆን በማሰብ ከሙያቸው ውጭ ስራውን በቅንነት የሚሰሩ ሰዎች መመደባቸውን አስረድተዋል።

የስራውን አካሄድ በተመለከተም በየመሃሉ ሂደቱ ስለሚገለጽ በዛ ደረጃ መገምገም እንደሚቻል ጠቅሰዋል።

ውይይት እየተደረገበት ያለው የትምህርት ፍኖተ ካርታ አንድን ቋንቋ በሌላ ክልል ማስተማር መልካም ነው የሚል እሳቤ የያዘና ይህ ጉዳይ በውይይት እየዳበረ የሚሄድ መሆኑንም አስረድተዋል።

ሃብት ማስመዝገብን በተመለከተም ከማስመዝገብ ባለፈ ሌብነትን የሚጠየፍ ዜጋ መፍጠር ምንጩ ያልታወቀ ሃብትን ለመከላከል ዋነኛ መፍትሄ ነው ብለዋል።

ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም የፕሮጀክት አስተዳደርና የዲዛይን ስራው ችግር እንደነበረበት አንስተዋል።

ከዚህ ጋር በተገናኘም የኮንትራት አስተዳደር ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አሰራር መጀመሩን አውስተዋል።

ይህም ሜቴክ ጀምሮ በማይጨርሳቸው ግዙፍ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን አቅሙ ላላቸው ኩባንያዎች ለመስጠት ያስችላልም ነው ያሉት።

የውጭ ምንዛሪ እና የድንበር ጉዳይ፥ የተመዘገበው ኢኮኖሚያዊ እድገት በሌሎች ዘርፎች ላይ በርካታ ለውጦችን ቢያመጣም በውጭ ምንዛሪ ግን እጥረት ማጋጠሙን አውስተዋል።

ኮንትሮባንድና የውጭ ምንዛሪ ግብዓቶች ከመንግስት ይልቅ ወደ ግለሰቦች መግባት፥ ለዘርፉ ዋነኛ ችግር መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከዚህ አንጻርም በቅንጅት መስራት፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም ከጎብኝዎች እና ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ ከሚላከው ገንዘብ የሚገኘውን ምንዛሪ በህግ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከድንበር ጋር በተያያዘም ከሱዳን አጎራባች በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢና በሱዳን በኩል ያለው የድንበር ወሰን መልክ ባለመያዙ ችግሮች መከሰታቸውን ገልጸዋል።

በቅርቡም በመሪዎች ደረጃ ውይይት ተደርጎ በሁለቱም በኩል ታጣቂዎች ከድንበር እንዲርቁና ጥበቃውን በጋራ ለማካሄድ ስምምነት ተደርሷልም ነው ያሉት።

የድንበር ማካለሉ ጉዳይም በድርድር የሚፈታ ይሆናል ያሉት በሰጡት ምላሽ።

በሶማሌ ክልል ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋር በተያያዘም የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፥ አቶ አብዲ ሙሐመድ ኦማር ጉዳይ ወደፊት በህግ የሚታይ አግባብ እንደሚታይ አንስተዋል።

መርማሪ ፖሊስ በመስቀል አደባባዩ ፍንዳታ ጥቅም ላይ ከዋለው ቦምብ ጋር ተመሳሳይ ቦምብ በተጠርጣሪ ቤት ውስጥ ማግኘቱን ገለፀ



በመስቀል አደባባዩ ፍንዳታ

(ኤፍ ቢ ሲ) በሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባዩ ላይ የተወረወረ አይነት ተመሳሳይ ቦምብ በተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ አስታወቀ።

መርማሪ ፖሊስ ዛሬ በተረኛ የጊዜ ቀጠሮን በሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ የደረሰበትን የምርመራ ደረጃ ለፍርድ ቤት ባስረዳበት ወቅት ተመሳሳይ ቦምብ ማግኘቱን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ ከሰኔ 16ቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ድጋፍ ሰልፍ ላይ የከቦምብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ በአማኒኤል ሆስፒታል ከአይምሮ ህመም በህክምና ላይ የምትገኘውን የህይወት ገዳን ምርመራን ማቋረጡንም በዛሬው ችሎት አብራርቷል።

በችሎቱ በቀዳሚነት የተጠርጣሪ በየነ ቡላና የአብዲሳ መገርሳን የተደረሰውን የምርመራ ደረጃ አዳምጧል።

መርማሪ ፖሊስም በርካታ የምርመራ ስራዎችን ማከናወኑን በመጠቆም ተጨማሪ የኤፍ ቢ አይ የቴክኒክ ምርመራ ውጤትን እና መሰል ማስረጃዎቸን ለመቀበል ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

የተጠርጣሪ አብዲሳ መገርሳ ጠበቃ በበኩላቸው የተጠረጠረበት ጉዳይ ስለፍንዳታው ለግብረ አበሮቹ ሪፖርት አድርገሃል ተብሎ ነው።

ረጅም ጊዜ ምርመራው የሚወስድ አይደለም ጉዳዩም ዋስትና የሚያስከለከል ባለመሆኑ በዋስ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የፖሊስን ተጨማሪ ጊዜ ተቃውመዋል።

ተጠርጣሪ በየነ ቡላ በበኩሉ እኔ በፍቼ ነው የተያዝኩት ሆን ተብሎ እኔን ለማጥቃት የሚደረግ ድርጊት ነው በማለት ከዘርና ከፖለቲካ ጋር አያይዘው ላቀረቡት አስተያየት ፍርድ ቤቱ በችሎት ህጋዊ ድርጅትን መዝለፍ አይፈቀድም ሲል ንግግራቸውን አስቁማል።

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎች ላይ የተገኘ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳለ መርማሪ ፖሊስ እንዲያበራራ ጠይቋል።

መርማሪ ፖሊስም ከፍተኛ አመራሮች የሚገኙበት የድጋፍ ሰልፍ በመሆኑ በዋናነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ለመግደል እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሰልጣኖች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የታቀደና የተሞከረበት ይህ ድርጊትን በ160 ንጹሃን ዜጎች ላይ የአካል ጉዳትና የሁለት ሰው ሞት እና ቤተሰቦቻቸውን ማሰብ ያሰፈልጋል ብሏል።

ይህ የወንጀል ድርጊት ከላይኛው አመራር እስከ ታቸኛው አመራር ድረስ ተሳትፎ ያለበት መሆኑን ፖሊስ ጠቅሷል።

በየነ ቡላን በተመለከተ ከሌሎች ከተጠረጠሩ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን ቦምቡን እንዴት እንደሚያፈነዱ በመነጋገር በማመቻቸት ቦምቡ እንዲፈነዳ ማስደረጉን የሚጠቁም ማስረጃ እንዳለው ገልጿል።

ሁለተኛ ተጠርጣሪ አብዲሳ መገርሳም ከቦምብ ፍንዳታው በኋላ ፍንዳታው ጉዳት ማን ላይ እንደደረሰና የቦምቡን ጉዳት ሁኔታ ለግብረ አበሮቹ ሪፖርት ማደረጉን የሚያመላከት ማስረጃ አለኝ ሲል ዋስትናቸውንም ተቃውሟል።

የሁለቱንም ጉዳይ የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ምርመራው ውስብስብና የወንጀል ድርጊቱ ከባድ ጊዜ የሚጠየቅ መሆኑን በመጥቀስ ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለመጨረሻ እንዲቀርብ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜን ፈቅዷል።

በሁለተኛ ደረጃ ችሎቱ የተመለከተው የእነ አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማና ባህሩ ቶላን ጉዳይ ሲሆን፥ መርማሪ ፖሊስ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ጋር አብራ ምርመራ ሲከናወንባት የነበረችው ህይወት ገዳ ጉዳይን ማቋረጡን አስታውቋል።

በተመሳሳይ የምራመራ ስራውን ማከናወኑን በመግለጽ ከኤፍ ቢ አይ የቴክኒክ ምርመራን እና መስል ማስረጃን ለማቀረብ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የአብዲሳ ቀነኔ ጠበቃ በበኩላቸው አብዲሳ የተያዘው ሰው ለመጠየቅ አቤት ሆስፒታል በሄደበት ጊዜ እንጂ ድርጊቱን አልፈፀመም ፖሊስ የድርጊቱ መፈጸምን የሚያሰረዳ ማስረጃ መዝገቡን አቅርቦ ሊያሳይ ይገባል ፖሊስ ምስክር እንዲሆነን የሚያቀርበው ጥያቄ ተገቢ አይደለም ሲሉ በዋስ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ጥያቄን ተቃውመዋል።

በተመሳሳይ ሌሎች ተጠርጣሪዎችም የተጨማሪ ጊዜን በመቃወም ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት የለንም በማለት ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የተጠርጣሪዎቹን የተጠረጠሩበት ድርጊት በማስረጃ መረጋገጡን ፖሊስ እንዲያሰረዳ በጠየቀው መሰረት ፖሊስ ጌቱ ግርማ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሰኔ 16 የመስቀል አደባባዩ የቦምብ ጥቃት ለማድረስ የተወረወረ አይነት ተመሳሳይ ቦምብ መገኘቱን ገልጿል።

አብዲሳ ቀነኔ ባለው የህክምና ሙያ ተጠቅሞ ቦምቡን አፈንድቶ በራሱ ላይም ጉዳት የደረሰበትን ለማስመለጥ አቤት ሆስፒታል ሄዶ በጀርባ በኩል ለማስመለጥ ነርሶችን ሲያግባባ እንደነበርና ለዚሀም ማስረጃ እንዳለው ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሮዎቹ ምንቡን ለማፈንዳት እንዴት፣ የትና በምን ሁኔታ የሚለውን ጉዳይ አስቀድመው መረጃ የተለዋወጡበትን ሆነ ከፈነዳ በኋላ የተለዋወጡበት መረጃም ሆነ ሌሎች ማስረጃዎች አሉኝ ሲል አብራርቷል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ምርመራው ውስብስብና የወንጀል ድርጊቱ ከባድ ጊዜ የሚጠየቅ መሆኑን በመጥቀስ ለመርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቀርብ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜን ፈቅዷል።

የምርመራ መዝገቡን ከሁለት ቀን በፊት አቀርቦ እንዲያሳይ አዟል።

በታሪክ አዱኛ

መጪው አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል ይከበራል- መንግሰት

መጪው አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል ይከበራል- መንግሰት

(ኤፍ.ቢ.ሲ) መጪው አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በዓሉ ከ25 ሺህ በላይ ህዝብ በሚገኝበት በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት እንደሚከበር ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን፥ መንግስት በሀገሪቱ ተስተውሎ የነበረውን ቀውስ በትክክለኛ መንገድ በመፍታት በህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ድጋፍና ትብብር የሪፎርም ስራዎችን በመስራት የለውጥ፣ የአንድነትና የይቅርታ ሂደት በመጀመሩ መጪውን አዲስ አመት በደማቅ ሁኔታ ለመቀበል አስፈልጓል ብለዋል በመግለጫቸው።

መጪውን አዲስ ዓመት በደማቅ ሁኔታ ማክበር ያስፈለገበት ምክንያት ሚኒስትር ዴኤታው ሲገልጹ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የነበረውን ችግር መፍታት መቻሉ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር ቤት ገብተው በሰላማዊ ሁኔታ ለመስራት መወሰናቸው፣ እንዲሁም የሀይማኖት መሪዎች የነበራቸውን ልዩነት ወደ አንድነት የቀየሩበት ይቅርታና አንድነት በተግባር የታየበት ወቅት በመሆኑ ነው ብለዋል።

በኢኮኖሚው መስክ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትም ኢንቨስትመንት በመሳብና የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በመቋቋም ችግሩን በፍጥነት ማስወገድ መቻሉንም አቶ ካሳሁን አንስተዋል።

እንዲሁም በዲፕለማሲው በኩልም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በተለይ ከኤርትራ ጋር የነበረውን ሻካራ ግንኙነት በመፍታት ወደ እርቅና ሰላም የተመጣበት ጊዜ ነውም ሲሉ አስረድተዋል።

ለረዥም ዓመታት ታስረው የነበሩ የፖለቲካ እስረኞችንም በመፍታት ሀገራዊ መግባባት የተፈጠረበት እንደሆም ገልጸዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጣውን የለውጥ ሂደት በመጪው ዓመትም በአዲስ ተስፋ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል ቃልን የማደስ መርሀ ግብር ለማከናወን በማሰብ በደማቅ ሁኔታ የአዲሱን ዓመት ዋዜማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

በእለቱም የኪነጥበብ ዝግጅቶችን ጨምሮ የአንድነትና የይቅርታን ጠቀሜታ የሚያጎሉ መልእክቶች እንደሚተላለፉም ሚኒስትር ደኤታው አቶ ከሳሁን አስታውቀዋል።

በአሉ በዋናነት በሚሊኒየም አዳራሽ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የሚከበር ቢሆንም መሪ ቃሉን በሚያሰርፅ መልኩ ከአዲሱ ዓመት በፊትና በኋላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቃል የማደስ ፕሮግራሞች ይከናወናሉ ሲሉም ተናግረዋል።

የሚዲያ ተቋማትም የመሪ ቃሉን ጽንሰ ሃሳብ በዝርዝር ለህብረተሰቡ በማስረዳት አዲሱ ዓመትን በተስፋና በአዲስ መንፈስ ልንቀበለው ይገባል ሱሉም አቶ ካሳሁን መልእክት ማስተላለፋቸውን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬም እየተሰቃዩ ነው - ቢቢሲ

በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬም እየተሰቃዩ ነው

ህልሟ ባህር አቆራርጦ ጣልያን መግባት ነበር። ከወራት በፊት ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ አቀናች። አስከትላም ወደ መተማ አቅንታ ሱዳን ወስጥ አራት ወራትን አሳለፈች።

እንደሷው ያሉ ስደተኞች በሰሀራ በረሀ ለሚያዘዋውር ግለሰብ ገንዘብ ከፍላ በረሀውን በመኪና አቋረጠች። ሊቢያ አንደደረሰች ደላላ ተቀበላት። ተቀብሎም ለሌላ ደላላ ሸጣት።

ሊቢያ ውስጥ ኢምወሊድ የሚባል አካባቢ እሷና ሌሎችም ስደተኞች ታሰሩ። "ገንዘብ ክፈሉ" እየተባሉ ይደበደቡ እንደነበረ ትናገራለች።

ከእስር ቤቱ ለመውጣት ከኢትዮጵያ ወይም ከሌላ ሀገርም ገንዘብ እንዲያስልኩ በማስገደድ ያሰቃዩዋቸው እንደነበረም ታክላለች።

ወጣቷን በስልክ ያነጋገርናት ሊቢያ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ሳለች ነው። ከእስር ቤቱ ኢንዛራ ወደሚባል ቦታ ከተወሰዱ በኃላም እንግልቱ እንደቀጠለ ለቢቢሲ ገልፃለች።

"ከተደፈሩ ሴቶች አንዷ እኔ ነኝ" ትላለች ከደረሰባት ሁሉ የከፋውን ስትናገር።

በርካታ ሴቶች እንደሷ ተደፍረዋል፤ ተደብድበዋል። የተገደሉ እንዳሉም ትናገራለች። ካሉበት መጠለያ ለማምለጥ የሚሞክሩ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰው ድብደባ የከፋ ነው።

"እንድንፈራ እኛ ፊት ነው እንዳይሞቱም እንዳይድኑ አድርገው ነው የሚቀጠቅጧቸው" ትላለች። ያሉበትን ሁኔታ የሚነግሩት አንዳችም አካል እንደሌለ ገልጻ፤ እንደ ሱዳን ያሉ ሀገሮች ዜጎቻቸውን መታደግ እንደቻሉ በንጽጽር ትናገራለች።




ከምትገኝበት መጠለያ ከሶስት ቃለ መጠይቅ በኋላ መውጣት እንደምትችል ቢነገራትም ለስምንት ወር ያህል ከቦታው መውጣት እንዳልቻለች ትገልጻለች።

"ሁለት ጊዜ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ሶስተኛ ነው የቀረሽ ተብዬ ስምንት ወር ሆነኝ" ትላለች።

ጊዜያዊ መጠለያው ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞች ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚደርስባቸው እንግልት የከፋ መሆኑን የምትናገረው እሷ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም በስልክ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ሌሎች ዜጎች ከማቆያው ወደ ኒጀር እንደተሰደዱና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ከማቆያው እንዲወስዳቸው በሚጠባበቁበት ወቅት ምግብና መጠጥ ማግኘት እንደሚቸገሩም ይናገራሉ።

ያላቸውን ገንዘብ በፖሊሶች እንደተዘረፉ ያገጋገረችን ወጣት ትገልጻለች። "ስልካችንን ወስደውብናል፤ ከሶማሌዎች ተውሰን ነው እናንተንም ማናገር የቻልነው" ትላለች።

በተመሳሳይ መጠለያ ውስጥ የሚገኘው ሌላ ኢትዮጵያዊ "አሁን ራሱ አንዱን ሌላ ቦታ ወስደው እየደበደቡት ነው" ይላል በፍርሀትና በስጋት ተሸብቦ።

እሱም ተመሳሳይ የመደብደብ እጣ እንዳይገጥመው ይሰጋል።

እሱና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ድብደባና ስቃይ እንደበረታባቸው "ያለሁበት ቦታ ለህይወቴ አስጊ ነው" በማለት ይናገራል።

የሚገኙት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ቢሆንም ከሊቢያ ፖሊሶች ድብደባ እንዳልዳኑ ይናገራል። ሴቶች ይደፈራሉ።

በድብደባው ምክንያት አርግዘው ያስወረዳቸውም አሉ።

ይህኛው ወጣት የተያዘው ከስምንት ወር በፊት ባህር ለማቋረጥ ሲሞክር ነበር። እሱና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ሊቢያ፣ ትሪፖሊ ውስጥ ኢንዛራ የሚባል ቦታ ይገኛሉ።

ሌላ ቢቢሲ ያናገራት ኢትዮጵያዊት ለወራት በመጠለያው ሲቆዩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መውጣት እንዳልቻሉ ትናገራለች። አንዳንድ ቀን ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው ይቀመጣሉ።

"ወንዶቹን 'ስራ አለ' ብለው ወስደው ይገርፏቸዋል፤ አንዱን ደግሞ የት እንዳደረሱት አናውቅም" ስትል መጠለያው ውስጥ ፖሊሶች መስለው የሚገቡ ደላሎች የሚያደርሱባቸውን ትናገራለች።

ጨምራም"ሊደፍሩን ሲመጡ እየጮህን ከራሳችን ላይ እያስወረድን ነው እንጂ እነሱ በኛ መጫወት ነው የሚፈልጉት" ትላለች።

ደላሎቹ ስደተኞችን ከመጠለያው እያስወጡ ይሸጧቸዋል። ከሊቢያ ወጥተው ባህር ለመሻገር ገንዘብ እንዲከፍሉ በመጠየቅም ያንገላቷቸዋል።


ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ከሚገኙበት መጠለያ ሶማሌዎች እየተለዩ ወደ ኒጀር ይወሰዳሉ። ኢትዮጵያውያን ወይም ኤርትራውያን ጥያቄ ሲያቀርቡ ግን ቤት ውስጥ ይቆለፍባቸዋል። 

ስደተኞቹ ኒጀር ውስጥ ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው በኃላ ወደተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች እንዲሻገሩ ይደረጋል።

የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ወደ ጊዜያዊ መጠለያው ሲሄዱ ስደተኞቹን እንዳያናግሩ እንደሚደረጉ ይናገራሉ።

ኢትዮጵያኑ "እንድትደርሱልን እንለምናለን" የሚሉትም ለዚሁ ነው።

ስለሁኔታው የጠየቅናቸው ተሰናባቹ የግብጽ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በሊቢያ እየተንገላቱ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት መጓጓዣ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።

ሰነዱን ለመዘጋጀት የሚያስፈልግ መረጃ ከቦታው የሚልክ ተወካይ ወይም አስተዳዳሪ አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰው ይናገራሉ።

"ማንነታቸውን የሚገልጽ ዝርዝር ማስረጃ ስለሌላቸው አንጠይቅም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ብቻ በቂ ነው" የሚሉት አምባሳደሩ፤ ስደተኞቹ ካሉበት ሆነው ፎቷቸውንና ስማቸውን ከላኩ መጓጓዣ ሰነድ እንደሚያዘጋጁላቸው ተናግረዋል።

"በቦታው ሁነኛ ሰው ስለሌለን በቀጥታ ማግኘት አንችልም፤ የበረሀ ጩኸት ነው የሚሆነው፤ ልንደርሳቸው የምንችለው በምናውቃቸው ሰዎች ወይም ተቋሞች አማካይነት ብቻ ነው" ይላሉ።