Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

መዝናኛ

ነጻ አስተያየት

ሙዚቃዎች

ስፖርት

ጥበብ

ዜና

ቪዲዮዎች

» » » የኢትዮጵያ ታዳጊብሄራዊ ቡድን ሚያዝያ 22ትን በናፍቆት ይጠብቃል

የኢትዮጵያ ታዳጊብሄራዊ ቡድን ሚያዝያ 22ትን በናፍቆት ይጠብቃል

የማሊ ብሄራዊ ቡድንን እግዳ ተከትሎ በአቋራጭ ጋቦን ለምታሰናዳው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከወዲሁ አንድ እግሩን ማስገባት የቻለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ታዳጊ ቡድን በአሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ እየተመራ ልምምዱን በአዲስ አበባ ስቴዲየም ቀጥሏል 

በቀናቶች ውስጥም ከጋቦን አየር ንብረት ጋር ተመሳሳይነት ባላቸው አዋሳ አሊያም አዳማ በመሄድ ልምምዱን እንደሚሰራ ተሰምቷል፡፡ 

ታዳጊ ብሄራዊ ቡድኑ አፍሪካ ዋንጫው ላይ መሳተፉን ለማረጋገጥ የፊታችን እሁድንም በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል፡፡ ፊፋ በስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ጣልቃ ገብነትን ተመልከቶ ማሊ ላይ የጣለውን ቅጣት ተከትሎ የማሊ መንግስት እስከ ሚያዝያ 22 ምላሽ ሰጥቶ የቀድሞ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊዎችን ወደ ቦታቸው ካልመለሰ ማሊን ለቀጣዮቹ 2 አመታት ከማንኛቸውም አለማቀፋዊ ውድድሮች ያግዳል፡፡ 

ይህንን ተከትሎም በ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ በመጨረሻው ማጣሪያ በማሊ በድምር ውጤት ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ የነበረችው ኢትዮጵያም በውድድሩ ለመሳተፍ ይሄንን ቀን በናፍቆት ትጠብቃለች፡፡

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply