Theme images by kelvinjay. Powered by Blogger.

Slider

መዝናኛ

ነጻ አስተያየት

ሙዚቃዎች

ስፖርት

ጥበብ

ዜና

ቪዲዮዎች

» » » የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ነገ እና ከነገ ወዲያ ቀጥሎ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ነገ እና ከነገ ወዲያ ቀጥሎ ይካሄዳል

የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ 25 ሳምንት ጨዋታ ነገ እና ከነገ በስቲያ ሲቀጥል ኢትዮጵያ ቡና ነገ በ9 ሰአት ወደ አዋሳ አቅንቶ በሁለተኛው ዙር ከፍተኛ መሻሻልን ካሳየው አዋሳ ከነማ ጋር በ9 ሰአት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ 

በሁለተኛው ዙር መጠነኛ መዳከም አሳይቶ የነበረው አዳማ ከነማም በአዲስ አባባ ስቴዲየም ባሳለፍነው ሳምንት ፋሲል ከነማን ከረታው አዲስ አበባ ከነማ ጋር ይጫወታል፡፡ 

ጅማ አባቡናን ባለቀ ሰአት በተቆጠረ ግብ በመርታት ዋንጫ ፉክክር ውስጥ ያለው ሲዳማ ቡና ከኤሌክትሪክ ጋር በ10›30 ሲጫወት ጅማ አባቡና ወላይ ዲቻን ጅማ ላይ ያስተናግዳል፡፡ 

አርባምንጭ ከነማ እና መከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታም ሌላኛው ተጠባቂ የሊጉ 25ኛ ሳምንት ጨዋታ ነው፡፡ የፈታችን ረቡዕ ደግሞ ደደቢት ድሬዳዋ ከነማን ሲገጥም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ በ10›30 በርካታ ጨዋታዎችን በአዲስ አበባ ስቴዲየም መርታት ከቻለው ፋሲል ከነማ ይጫወታሉ፡፡ 

የዕለቱ ተጠባቂ እና ወሳኝ ጨዋታ ደግሞ በወልዲያ ሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲን ስቴዲየም በወልዲያ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚደርግ ሲሆን ፈረሰኞቹ የፊታችን ረቡዕ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ በምድብ ድልድል ከማን ጋር እንደሚገኛኙ ከማወቃቸው በፊት የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ነው፡፡

«
Next
Newer Post
»
Previous
Older Post

No comments:

Leave a Reply